Saturday, October 28, 2017

ሰማእትነት አያምልጥህ

ለመላው አዲስ አበባ ዙሪያና የንደር ነዋሪ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምእመናን የቀረበ ብጹአን መነኮሳትን ከእስር የማስፈታት ጥሪ!
v  “ በዚያን ጊዜ ለመከራ አሳልፈው ይሰጡአችሗል ይገድሉአችሁማል ስለ ስሜም በአሕዛብ ሁሉ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ።”  የማቲዎስ ወ. ም-24፣ቁ-9
               
 
 
 
           ፍጹም ልትሆን ብትፈልግ ያለህን ሽጠህ ለድሆች ሰተህ ተከተለኝ ፤ በሚለው አምላካዊ ትዛዝ መሰረት ሀብትና ንብረታቸውን እና ቤተሰባቸውን ትተው በታላቁ ዋልድባ ገዳም መንነው በፆም እና በፀሎት የፀኑትን ብጹአን አባቶች ገዳማችን የመፍረስ አደጋ አጋጥሞታል ብለው ለምእመናኑ በማሳወቃቸው ምክንያት በንደር እና በአዲስ አበባ ቂሊንጦ እስር ቤት በመሰቃየት ላይ ናቸው። በአዲስ አበባ  እና በንደር የምትኖሩ ምእመናን እደቀደሙት ሰማእታት አባቶቻችሁ ሰማእትነት ለመቀበል ከዚህ የተሻለ እድል አታገኙም። በዚሁ መሰረት ከዚህ ጊዜ ጀምሮ የሰማህ ላልሰማ እያሳወክ እንደጥምቀት እና መስቀል በነቂስ በመውጣት አዲስ አበባ ወደ ቂሊንጦ እና  ንደር እስርቤት በመትመም ብጹአን መነኮሳትን እንድናስፈታ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስቲያኖች ኅብረት ጥሪ ቀርቦልሀል።
 
v  “ ወደ ሞት የሚነዱትን ታደግ ሊታረዱ የተወሰኑትን አድን። እንሆ ይህን አላውቅም ብትል፤ ልቦችን የሚመረምር እርሱ አያስተውልምን? ነፍስህንም የሚመለከት እርሱ አያውቅምን? ለሰውስ ሁሉ እንደ ስራው አይመልስለትምን?  መጽሐፈ ምሳሌ ም.29 ቁ.11