ለመላው አዲስ አበባ
ዙሪያና የጐንደር ነዋሪ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምእመናን የቀረበ ብጹአን
መነኮሳትን ከእስር የማስፈታት ጥሪ!
v
“ በዚያን ጊዜ
ለመከራ አሳልፈው ይሰጡአችሗል ይገድሉአችሁማል ስለ ስሜም በአሕዛብ ሁሉ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ።” የማቲዎስ ወ. ም-24፣ቁ-9
ፍጹም
ልትሆን ብትፈልግ ያለህን ሽጠህ ለድሆች ሰተህ ተከተለኝ ፤ በሚለው አምላካዊ ትዛዝ መሰረት ሀብትና ንብረታቸውን እና ቤተሰባቸውን
ትተው በታላቁ ዋልድባ ገዳም መንነው በፆም እና በፀሎት የፀኑትን ብጹአን አባቶች ገዳማችን የመፍረስ አደጋ አጋጥሞታል ብለው ለምእመናኑ
በማሳወቃቸው ምክንያት በጐንደር እና በአዲስ
አበባ ቂሊንጦ እስር ቤት በመሰቃየት ላይ ናቸው። በአዲስ አበባ እና
በጐንደር የምትኖሩ ምእመናን እደቀደሙት ሰማእታት አባቶቻችሁ
ሰማእትነት ለመቀበል ከዚህ የተሻለ እድል አታገኙም። በዚሁ መሰረት ከዚህ ጊዜ ጀምሮ የሰማህ ላልሰማ እያሳወክ እንደጥምቀት እና
መስቀል በነቂስ በመውጣት አዲስ አበባ ወደ ቂሊንጦ እና በጐንደር እስርቤት በመትመም ብጹአን መነኮሳትን እንድናስፈታ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስቲያኖች ኅብረት ጥሪ ቀርቦልሀል።
v “ ወደ ሞት የሚነዱትን ታደግ ሊታረዱ የተወሰኑትን አድን። እንሆ
ይህን አላውቅም ብትል፤ ልቦችን የሚመረምር እርሱ አያስተውልምን? ነፍስህንም የሚመለከት እርሱ አያውቅምን? ለሰውስ ሁሉ እንደ ስራው
አይመልስለትምን? መጽሐፈ ምሳሌ ም.29 ቁ.11