Saturday, October 28, 2017

ሰማእትነት አያምልጥህ

ለመላው አዲስ አበባ ዙሪያና የንደር ነዋሪ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምእመናን የቀረበ ብጹአን መነኮሳትን ከእስር የማስፈታት ጥሪ!
v  “ በዚያን ጊዜ ለመከራ አሳልፈው ይሰጡአችሗል ይገድሉአችሁማል ስለ ስሜም በአሕዛብ ሁሉ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ።”  የማቲዎስ ወ. ም-24፣ቁ-9
               
 
 
 
           ፍጹም ልትሆን ብትፈልግ ያለህን ሽጠህ ለድሆች ሰተህ ተከተለኝ ፤ በሚለው አምላካዊ ትዛዝ መሰረት ሀብትና ንብረታቸውን እና ቤተሰባቸውን ትተው በታላቁ ዋልድባ ገዳም መንነው በፆም እና በፀሎት የፀኑትን ብጹአን አባቶች ገዳማችን የመፍረስ አደጋ አጋጥሞታል ብለው ለምእመናኑ በማሳወቃቸው ምክንያት በንደር እና በአዲስ አበባ ቂሊንጦ እስር ቤት በመሰቃየት ላይ ናቸው። በአዲስ አበባ  እና በንደር የምትኖሩ ምእመናን እደቀደሙት ሰማእታት አባቶቻችሁ ሰማእትነት ለመቀበል ከዚህ የተሻለ እድል አታገኙም። በዚሁ መሰረት ከዚህ ጊዜ ጀምሮ የሰማህ ላልሰማ እያሳወክ እንደጥምቀት እና መስቀል በነቂስ በመውጣት አዲስ አበባ ወደ ቂሊንጦ እና  ንደር እስርቤት በመትመም ብጹአን መነኮሳትን እንድናስፈታ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስቲያኖች ኅብረት ጥሪ ቀርቦልሀል።
 
v  “ ወደ ሞት የሚነዱትን ታደግ ሊታረዱ የተወሰኑትን አድን። እንሆ ይህን አላውቅም ብትል፤ ልቦችን የሚመረምር እርሱ አያስተውልምን? ነፍስህንም የሚመለከት እርሱ አያውቅምን? ለሰውስ ሁሉ እንደ ስራው አይመልስለትምን?  መጽሐፈ ምሳሌ ም.29 ቁ.11
 
 
 


Sunday, April 2, 2017

በኢሕአዲግ ባለስልጣናት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ላይ የደረሰ የዘር ፍጅትና ጥቃት


 

      ኢሕአዲግን የመሰረቱት ግለሰቦች አስቀድመው በ1960ቹ ዓ.ም በተማሪው እንቅስቃሴ ወቅት የማርክስ ሌኒን የፖለቲካ አማኝ የነበሩ የትግራይ ተወላጅ ሲሆኑ፤ በዚሁ እምነት መሰረት በፀረ ሀይማኖትን አስተሳሰብ በመለከፋቸው በተለይ ለኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ከፍተኛ ጥላቻ አላቸው። ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን እና ተከታዮችን በሀገሪቱ ብቸኛ ተጠቃሚ አድርጎ የሚሰብከው  የ1960ዎቹ የነበረ ዋለልኝ መኮንን የሚባለው ወጣት (The Question of Nationalities in Ethiopia) በሚለው የእንጊልዘኛ ጽሑፉ ላይ በጊዜው የነበሩ ወጣቶች ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይ ከፍተኛ ጥላቻ  እንደነበራቸው ያሳያል።
       በጽሑፍ ላይ እንደታየው ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እና ተከታዮቿ በኢትዮጵያ ውስጥ ምንም አይነት የፖለቲካም ሆነ የኢኮኖሚ የበላይነት ሊኖራቸው እንደማይገባ ይሰብካል። ይህን የወያኔን ጸረ ኦርቶዶክስ አቋም ምቹ ሁኔታ የፈጠረላቸው ጸረ ኦርቶዶክስ ፕሮቴስታንት እና ሙስሊም ባለስልጣናት ስልጣናቸውን በመጠቀም በኦርቶዶክስ ክርስቲያኑ ላይ ከፍተኛ የዘር ፍጅት ፈጽመዋል።  በተግባር እንደሚታየው ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ከፖለቲካው ስርአት በተቀነባበረ መልኩ ሲገለሉ በኢኮኖሚውም እረገድ በአዋጅ ንብረታቸውን ተወርሰው አብዛኛውም ምእመናን በድሕነት እንዲማቅቁ ተደርገው በራሳቸው መሬትና ባፈሩት ንብረት ሌሎች ሲንደላቀቁበት ይታያል።
 
 


 
       (Marxism and the National Question by J.V. Stalin) መጽሐፍ ላይ እንደሚለው “የአንድን ሀገር ሕዝብ እንድ ከሚያደርጋቸው ነገር አንዱ ተመሳሳይ ቋንቋ ተናጋሪዎች መሆናቸው ነው” ይላል፤ ወያኔ ይህንን አስተሳሰብ በመከተል በኢትዮጵያ ውስጥ የቋንቋ ማንነት ከሌላው ማንነት በተለየ የበላይ አድርጎ በመስበክ የብዙ ቋንቋ ተናጋሪ ሀገር ኢትዮጵያን እንደ አንድ ሀገር ባለመቁጠር በኢትዮጵያ ሕዝብ ታሪክ ያልነበረ ቋንቋን መሰረት ያደረገ ስርአት መንግስትና ሀገር ለማስፈን እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

         ከላይ የተጠቀሰውን አላማውን ለማሳካት በዋናነት የሀይማኖት አንድነት እና ሕብረት እንቅፈት እንደሆኑበት ተገንዝቧል። በዮሐንስ ራእይ ም.13 ከ ቁ.6 እንዲሕ ተብሎ እንደተጸፈው “ እግዚአብሔርንም ለመሳደብ ስሙንና ማደሪያውንም በሰማይም የሚያድሩትን ሊሳደብ አፍን ከፈተ። ቅዱሳንንም ይዋጋ ዘንድ ድልም ያደርጋቸው ዘንድ ተሰጠው በነገድና በወገንምበቋንቋም በሕዝብም ሁሉ ላይ ስልጣን ተሰጠው። ከዓለምም ፍጥረት ጀምሮ በታረደው በግ ሕይወት መጽሐፍ ስማቸው ያልተጻፈ በምድር የሚኖሩ ሁሉ ይሰግዱለታል። ጆሮ ያለው ቢኖር ይስማ።”  ይሕ የሚያሳየን የዳቢሎስ መንፈስ በመሪዎች ላይ በማደር በቋንቋና በነገድ እየከፈለ ያልተጠመቁትንና የክርስቶስን ስጋና ደሙን ያልተቀበሉትን እንደሚገዙለትና ክርስትናን ተቀብለው ነገር ግን በቋንቋና በነገድ ወገንተኝነት የሳቱትና ለዳብሎስ የተገዙለት ስማቸው ከሕይወት መጽሐፍ እንደሚደመስ ነው።
        ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የሰው ልጅ በዘሩ፣ በቋንቋው፣ በባሕሉ፣ እና በሀገሩ የተለያየ ማንነት ቢኖረውም የሀይማኖቱ ማንነት ከሁሉ የበለጠ ማንነት ነው ብላ ታስተምራለች። ይህንንም እምነት የማያምን ክርስቲያን ክርስቲያን ተብሉ አይጠርም፤ እራሱንም ከክርስቲያን ሕብረት የወጣና የተለየ ይሆናል። ይህ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እምነትና ሕግ በዳብሎስ መንፍስ ለሚመራው የወያኔ መሪዎች እራስ ምታት ስለሆነባቸው ገና ጫካ ሳሉ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ጠላት አድርገው በመውስድ ከቻሉ በቀጥታ የጥፋት እርምጃ በመውሰድ ካልቻሉ ከቤተክርስቲያን በእምነታቸው የተለዩና የተወገዙ አፍቃሪ ካቶሊኮችን በቤተክርስቲያን አስርጎ በማስገባት ከፍተኛውን የመንፈሳዊ አስተዳደር ቦታ በማስያዝ ቤተክርስቲያንን አቅም አልባና ደካማ በማድረግ እና ምእመናኑ ለመንግስት እንዲገዙ አድርገዋል።
       ዛሬ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አስተዳደር ሙሉ በሙሉ በሕውሀት ስር በመሆኑ የቤተክርስቲያን ንብረት በመዝረፍ እና እውነተኛ ምእመናንን በማሳደድ ላይ ይገኛል። ሊላው ሕውሀት የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን  እና ምእመናንን ጠላት አድርጎ በመውሰዱ ምእመናንን በተለያየ ጊዜ የተለያየ ስም በመስጠት የጭፍጨፋ እርምጃ በተቀነባበረ መልኩ ተወስዶበታል እየተወሰደም ይገኛል።
 
 
 

          በፈረንጆች አቆጣጠር በ1994 በኢትዮጵያ ከጠቅላላው የሕዝቡ ቁጥር 50.6 % ኦርቶዶክስ ክርስቲያን የነበረ ሲሆን ከ 13 ዓመት በሆላ በተደረገ የሕዝብ ቆጠራ በ2007 በ 7.1% አንሶ 43.5% ሆኖል ልዩነቱን በቁጥር ስንቀይረው 2282973 ብዛት ያለው ሕዝብ ይሆናል ይህም የሆነው ወያኔ ስልጣን ከያዘ ከ3 ዓመት የጀምሮ እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ከ1986 – 1999 ዓ.ም ሲሆን በነዚ ጊዜያቶች በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ላይ ከፍተኛ   የጅምላ ጭፍጨፋ፣ እስራት፣ ከመሬቱ ማፈናቀል፣ የመሳሰሉት እርምጃዎች ሁሉ የተወሰዱበት ጊዝያት ነበሩ።
 

 

 




 





       ለምሳሌ ቦታዎችን ብንጠቅስ፦ የእስልምና የክልል ባለስልጣናትን በመጠቀም በሐረር፣ በቤንሻንጉል፣ እና በአርሲ፤ የፕሮቴስታንት እና የካቶሊክ የክልል ባለስልጣናትን በመጠቀም በወለጋ እና በጉራ ፈርዳ ላይ የተደረጉት ጭፍጨፋዎችና ማፈናቀሎች በሙሉ በኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ላይ የተፈፀሙ ናቸው። ይህንን እውነታ የሚያጠናክር በ1994 እና በ2007 በሀገሪቱ በዋና ዋና ክልሎች የእምነቶች አማኝ ቁጥር በፐርሰንት እንደተቀመጠው የኦርቶዶክስ ክርስቲያኑ ቁጥር በከፍተኛ ቁጥር  እንዳሽቆለቆለ በቂ ማሳያ ነው።