- የቀድሞ የኢትዮጵያ
ስርአተመንግስት እና ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን
በኢትዮጵያ የመንግሰት ስርአት
ከክርሰትና በፍት የቆየ ሲሆን የንጉሰ ነገስቱ ሀይማኖት ክርስትናን
ከተቀበለበት ጊዜ አንስቶ ነገስታቱ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን በማስፋፋት ትልቅ ሚና ነበራቸው። የክርስትና ህግጋትና አስተምሮ በመንግስት
ስርአት እና ባሕል ውስጥ ተዋሕደው ይታያሉ።
- የጣልያን ወረራ
እና ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን
በ1928 ዓ.ም ጣልያን ኢትዮጵያን ሲወር ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ከመንግስት ጋር ያላትን ቁርኝት በሚገባ ስለተረዳ
ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን በጠላትነት በመፈረጅ፤ ቤተክርስቲያን ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል።
በጠቅላላው ፋሺስት ኢጣልያ በአምስት አመት ወረራው
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች፣ ካህናት፣ መነኮሳት ላይ ያደረሰው
ጭፍጨፋ እጅግ ዘግናኝ ነበር፡፡ በመነኮሳት ላይ እና በካህናት ላይ ብቻ
የደረሰውን ስንመለከት፤
1. በሐምሌ 22 ቀን
1929 ዓ.ም አቡነ ጴጥሮስ በ አ.አ ከተማ ተገደሉ፡፡
2. በኅዳር 24 ቀን
1929 ዓ.ም አቡነ ሚካኤል በጎሬ ላይ ታረዱ፡፡
3. ግንቦት 23 ቀን
1929 ዓ.ም የዜና ማርቆስ ካህናት በቅዳሴ ላይ እንዳሉ 43 መነኮሳት ተገድለዋል፡፡
4. በሰኔ 12 ቀን
1929 ዓ.ም የዝቋላ ገዳም መነኮሳት በማስታኮት ላይ እንዳሉ 211 መነኮሳት ታረዱ ፡፡
5. በሰኔ 3 ቀን
1929ዓ.ም የምድረ ከብድ ገዳም 60 መነኮሳት ታረዱ፡፡
6. በሰኔ 15 ቀን
1929 ዓ.ም የአሰቦት ደብረ ወገግ መነኮሳት 91 ታረዱ፡፡
7. በኅዳር 25 ቀን
1929 ዓ.ም የአዲስ ዓለም ካህናት በአሰቃቂ ሁኔታ ታረዱ ብዛታቸው 135 ነበር፡፡
8. ጥቅምት 17 ቀን
1929 ዓ.ም በደብረ ዳሞ ገዳም 416 መነኮሳት ታርደዋል፡፡
9. መጋቢት 16 ቀን
1929 ዓ.ም የማህበረ ሥላሴ ገዳም መነኮሳት ጠባቂዎች ሳይቀሩ 513 ተገደሉ በዚህም ቀን የደብረ አባይ ገዳም ተመዘበረ፡፡
10. በሚያዝያ 18 እና
20 ቀን 1929 ዓ.ም የመርጦለማርያምና የተድባበ ማርያም ካህናት 363 በጭካኔ ታረዱ፡፡
11. በሐምሌ 29 ቀን
1929 ዓ.ም የጎንደር ሊቃውንት ተለቅመው ከታሰሩ በኃላ ግማሾቹ ተገደሉ የተቀሩት ወደእስር ተወሰዱ፡፡
12. የካቲት 18 ቀን
1929 ዓ.ም የየካ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ታላላቅ 11 ሊቃውንት ተጠርተው ስቃይ ወዳለበት ቦታ ተወሰደው ታሠሩና ግማሾቹ
ተገደሉ፡፡
ይህ በታላላቅ ደብራትና ገዳማት ላይ የተፈጸሙ እና ተመዝግበው የሚታወቁ
ሲሆኑ ሳይመዘገቡ የቀሩ ብዙ እንዳሉ የሚገመት ሲሆን የሟቾቹም ቁጥር ከዚህም ይበልጣል፤ ከዚህም ጋር በተያያዘ በአምስት
ዓመት ውስጥ
ከ2000 በላይ ቤተክርስቲያናት
ተቃጠልዋለል፡፡
ፋሺስት ኢጣልያ በተከተላው
የከፋፍለ ግዛ ፖሊው የእስልምና ተከታይ ኢትዮጵያውያንን ከክርስቲያኑ የኢትዮጵያ መንግስት ነፃ ለማውጣት የመጣ አድርጎ ይሰብክ ስለነበር
በወቅቱ ስብከቱን ያመኑ 12ሺ የሙስሊም ጦር ከጎኑ ማሰለፍ ችሎ ነበር።
- የአፄ ኃ/ሥላሴ መንግስት እና
ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን
አፄ ኃ/ሥላሴ አፍቃሪ
ምእራባውያን በመሆናቸው የተነሳ ኢትዮጵያን በተራማጅ እስተሳሰብ መርቶ ሕዝቡን ምእራባዊ ባሕል፣ እምነት እና አስተሳሰብ እንዲኖረው
ገና እልጋ ወራሽ ከነበሩበት ጊዜ አንስቶ ሲሰሩበት ነበር። በጊዘው ለነበረው የአለም መንግስታት ማሕበር ኢትዮጵያን አባል ለማረግ
በፈረንሳይ ቋንቋ በድብቅ በጻፍት ደብዳቤ ላይ ለረጅም ጊዜ የኖረውን ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ከመንግስት ግኑኝነት እንደሚነጥሉ
ቃል በመግባት ነበር።
አፄ ኃ/ሥላሴ ኦርቶዶክስ
ቤተክርስቲያን በስም እንዳለች ሆና ስርአቷ ግን ፍፁም የካቶሊክን መንገድ እንድትከተል እንዳደረጉ ብዙ አባቶች ይናገራሉ። ለዚህም
ማስረጃ አፄ ኃ/ስላሴ ስልጣን ከያዙ በሆላ የተገነቡ ቤተክርስቲያናት እና የቤተክርስቲያናት ስእላት
ካቶሊካዌ ሆነዋል።
ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እራሷን
ችላ ጳጳሳትን እንድትሾም እና ሲኖዶስ እንዲኖራት የተሰራው ስራ ችግሮች የሞሉትና አንዳዶቹ የቤተክርስቲያንን ስርአት የጣሱ ናቸው።
ለምሳሌ፦ ሐዋርያት በ(ሐዋርያት ስራ ም. 6 ቁ.2-6) እንዳዘዙት ጳጳስቱ በቤተክርስቲያኖ ውስጥ የመንፈሳዊውን ስራ ብቻ መስራት
ሲገባቸው፤ የቤተክርስቲያን ስጋዌ ስርዎች በምእመናን በተመረጡ ሰዎች መሰራት ሲገባው ትዛዙን ወደጎን በመተው ጣልቃ ገብተዋል። እንዲሁም
ሐዋርያትን የሚወክሉ ብፁዐን ጳጳሳት ለአገልግሎታቸው የደሞዝ ክፍያ እንዲኖራቸው መደረጉ በማቴዎስ ወንጌል ም.19 ቁ.21-22 እንደተጻፈው
“ ፍጹም ልትሆን ብትወድ ሂድና ያለህን ሸጠህ ለድሆች ስጥ መዝገብም በሰማያት ታገኛለህ መጥተህም ተከተለኝ” የሚለውን የእግዚአብሔርን
ቃል የጣሰ ነው።
በአጠቃላይ አፄ ኃ/ሥላሴ በዘመናዌ ትምሕርት ሰበብ ትውልዱን የሀገሩን ታሪክ፣
ማንነቱን እና ሀይማኖቱን እንዳያውቅ በመደረጉ በተለይ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እንድትዳከም ሆኖዋል።
- ማርክስ ሌኒስት
የፀረ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እንቅስቃሴ
የማርክስ ሌኒስት አዲሱ ሪወትአለም
ሀይማኖትን በፅኑ የሚቃወም እንደመሆኑ በሌሎች ሀገራት እንደታየው ሁሉ በኢትዮጵያም ሀይማኖትን የእድገት ጸር አድርጎ ፈርጇል፤ በተለይ
ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን እና ተከታዮችን በሀገሪቱ ብቸኛ ተጠቃሚ አድርጎ የሚሰብከው የ1960ዎቹ የነበረ ዋለልኝ መኮንን የሚባለው ወጣት (The
Question of Nationalities in Ethiopia) በሚለው የእንጊልዘኛ ጽሑፉ ላይ በጊዜው የነበሩ ወጣቶች ኦርቶዶክስ
ቤተክርስቲያን ላይ ከፍተኛ ጥላቻ እንደነበራቸው ያሳያል።
በጽሑፍ ላይ እንደታየው ኦርቶዶክስ
ቤተክርስቲያን እና ተከታዮቿ በኢትዮጵያ ውስጥ ምንም አይነት የፖለቲካም ሆነ የኢኮኖሚ የበላይነት ሊኖራቸው እንደማይገባ ይሰብካል።
ለዚም ይመስላል አሁን በተግባር እንደሚታየው ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ከፖለቲካው ስርአት በተቀነባበረ መልኩ ሲገለሉ በኢኮኖሚውም
እረገድ በአዋጅ ንብረታቸውን ተወርሰው አብዛኛውም ምእመናን በድሕነት እንዲማቅቁ ተደርገው በራሳቸው መሬትና ባፈሩት ንብረት ሌሎች
ሲንደላቀቁበት የሚታየው።
- የደርግ መንግስትና
ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን
የደርግ መንግሰት የፀረ ኦርቶዶክስ
ቤተክርስቲያን ስብከት ሰለባ የሆነ ስርአት ሲሆን፤ በቀጥታና በግልጽ ቤተክርስቲያኗ ላይ እና ምእመናንኑ ላይ ከፍተኛ በደል አድርሷል።
ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የመሬት ይዞታና የነበራትን ንብረቶች ከመዝረፍ አልፎ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖችን በጠላትነት በመፈረጅ በኢኮኖሚ
ለማደሕየት መሬታቸውን፣ መኖርያ ቤታቸውን እና ሕንጻዎቻቸውን በተቀነባበረ መልኩ ዘርፋል። አድሀሪ እና ፀረ አብዮት ብሉ ኦርቶዶክስ
ክርስቲያኑን በመፈረጅ ከፍተኛ የጅምላ ፍጅት ፈጽሟል።
- የሕወሀት ፖለቲካና
ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን
ሕውሀትን የመሰረቱት ግለሰቦች
አስቀድመው በ1960ቹ ዓ.ም በተማሪው እንቅስቃሴ ወቅት የማርክስ ሌኒን የፖለቲካ አማኝ የነበሩ የትግራይ ተወላጅ ሲሆኑ፤ በዚሁ
እምነት መሰረት በፀረ ሀይማኖትን አስተሳሰብ በመለከፋቸው ለኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ከፍተኛ ጥላቻ አላቸው። (Marxism
and the National Question by J.V. Stalin ) መጽሐፍ ላይ እንደሚለው “የአንድን ሀገር ሕዝብ እንድ ከሚያደርጋቸው
ነገር አንዱ ተመሳሳይ ቋንቋ ተናጋሪዎች መሆናቸው ነው” ይላል፤ ይህንን አስተሳሰብ በመከተል በኢትዮጵያ ውስጥ የቋንቋ ማንነት ከሌላው
ማንነት በተለየ የበላይ አድርጎ በመስበክ የብዙ ቋንቋ ተናጋሪ ሀገር ኢትዮጵያን እንደ አንድ ሀገር ባለመቁጠር በኢትዮጵያ ሕዝብ
ታሪክ ያልነበረ ቋንቋን መሰረት ያደረገ ስርአት መንግስትና ሀገር ለማስፈን እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።
ከላይ የተጠቀሰውን አላማውን ለማሳካት በዋናነት የሀይማኖት አንድነት እና ሕብረት
እንቅፈት እንደሆኑበት ተገንዝቧል፤ በተልይ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የሰው ልጅ በዘሩ፣ በቋንቋው፣ በባሕሉ፣ እና በሀገሩ የተለያየ
ማንነት ቢኖረውም የሀይማኖቱ ማንነት ከሁሉ የበለጠ ማንነት ነው ብላ ታስተምራለች። ይህንንም እምነት የማያምን ክርስቲያን ክርስቲያን
ተብሉ አይጠርም፤ እራሱንም ከክርስቲያን ሕብረት የወጣና የተለየ ይሆናል። ይህ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እምነትና ሕግ ለሕውሀቶች
እራስ ምታት ስለሆነባቸው ገና ጫካ ሳሉ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ጠላት አድርገው በመውስድ ከቻሉ በቀጥታ የጥፋት እርምጃ በመውሰድ
ካልቻሉ ከቤተክርስቲያን በእምነታቸው የተለዩ አፍቃሪ ካቶሊኮችን በቤተክርስቲያን እስርጎ በማስገባት ከፍተኛውን ቦታ በማስያዝ ቤተክርስቲያንን
አቅም አልባና ደካማ በማድረግ እና ምእመናኑ ለወያኔ ስርአት እንዲገዙ አድርገዋል።
ዛሬ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን
አስተዳደር ሙሉ በሙሉ በሕውሀት ስር በመሆኑ የቤተክርስቲያን ንብረት በመዝረፍ እና እውነተኛ ምእመናንን በማሳደድ ላይ ይገኛል።
ሊላው ሕውሀት የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እና ምእመናንን ጠላት አድርጎ
በመውሰዱ ምእመናንን በተለያየ ጊዜ የተለያየ ስም በመስጠት የጭፍጨፋ እርምጃ በተቀነባበረ መልኩ ተወስዶበታል እየተወሰደም ይገኛል።
ሕውሀት ለ25 ዓመት ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖችን ሲጨፈጭፍ የተለያዩ የማደናገሪያ ዘዲዎችን በመጠቀም ሲሆን ከነዚሁስጥም ሁለቱን እንደሚከተለው
ቀርቦል፦
1- ከጠቅላላው የሕዝቡ ቁጥር 81.5 % ኦርቶዶክስ የሆነውን የአማራውን ሕዝብ
ማጥፋት ኦርቶዶክስን ማጥፋት ነው በማለት የጅምላ ጭፍጨፋ፣ እስራት፣ ከመሬቱ ማፈናቀል፣ የመሳሰሉት እርምጃዎች ሁሉ ተወስደዋል እየተወሰዱም
ይገኛሉ። ይህንን እውነት የሚያጠናክርልን በአማራ ስም ጭፍጨፋ በተደረጉባቸው የሀገሪቱ ክፍሎች ሁሉ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያናትም
ተቃጥለዋል አገልጋይ ካሕናትም ታርደዋል።
ለምሳሌ ቦታዎችን ብንጠቅስ፦ የእስልምና
የክልል ባለስልጣናትን በመጠቀም በሐረር፣ በቤንሻንጉል፣ እና በአርሲ፤ የፕሮቴስታንት እና የካቶሊክ የክልል ባለስልጣናትን በመጠቀም
በወለጋ እና በጉራ ፈርዳ ላይ የተደረጉት ጭፍጨፋዎችና ማፈናቀሎች በሙሉ በኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ላይ የተፈፀሙ ናቸው። ይህንን
እውነታ የሚያጠናክር በ1994 እና በ2007 በ13 ዐመታት ውስጥ በሀገሪቱ በዋና
ዋና ክልሎች የእምነቶች አማኝ ቁጥር በፐርሰንት እንደተቀመጠው የኦርቶዶክስ ክርስቲያኑ ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ እንዳሽቆለቆለ ያሳያል።
ከታች
በቻርቱ ላይ እንደምንመለከተው በ1994 እና በ2007 በአማራው
ክልል የእምነቶች አማኝ ቁጥር በ ፐርሰንት ቀርቦል፤ በ2007 የኦርቶዶክስ ክርስቲያኑ ብዛት ከ1994 በ3% ቀንሶ ይገኛል።
ከታች በቻርቱ ላይ እንደምንመለከተው በ1994 እና በ2007 በኦሮሚያ ክልል የእምነቶች አማኝ ቁጥር በ ፐርሰንት ቀርቦል፤ በ2007
የኦርቶዶክስ ክርስቲያኑ ብዛት ከ1994 10.9% ቀንሶ
ይገኛል።
ከታች በቻርቱ ላይ እንደምንመለከተው በ1994 እና በ2007 በደቡብ
ክልል የእምነቶች አማኝ ቁጥር በ ፐርሰንት ቀርቦል፤ በ2007 የኦርቶዶክስ ክርስቲያኑ ብዛት ከ1994 በ 7.7% ቀንሶ
ይገኛል።
2- ሕውሀት 90% በላይ ኦርቶዶክስ ከሚኖርበት የትግራይ ክፍለ ሀገር በመውጣቱ
ባለስልጣናቱ ምንም እንኳን እምነቱ ባይኖራቸውም ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይ የጥፍት እርምጃ ሊወስዱ አይችሉም የሚል አስተሳሰብ
በሕዝቡ ውስጥ እንዲፈጠር የፕሮፓጋንዳ ስራ ሰርተዋል። ባሳለፍነው
25 ዓመታት ውስጥ የተቃጠለው ቤተክርስቲያንና ገዳማት ብዛት እና በጅምላ የተጨፍጨፉት ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ብዛት ሲታይ ከሱማሌ
ወይም ከሱዳን መንግስት በኩል የተፈፀመ ቢሆን ኖሮ ያለምንም ማመታት ሀይማኖታችንን ሊያጠፉ ነው ብለን እንከስ ነበር፤ ሆኖም ግን
ድርጊቱ የሚፈጸመው በውስጣችን ባሉ እና ለዛውም ስማቸው ገ/መስቀል
እና ገ/ማርያም ተብለው በሚጠሩ ባለስልጣናት በመሆኑ እስከዛሬ ድረስ ክሱን አስቸጋሪ አድርጎታል።
እውነታው ግን ከታሪክ እንደምናየው በ1600 ክፍለ ዘመን አካባቢ በአፄ
ሱስንዮስ አማካኝነት ኢትዮጵያን ካቶሊክ የማድረግ ሙከራ ከከሸፈ በሆላ ካቶሊኮች ከኢትዮጵያ እንዲባረሩ ሲደረጉ አልፎንሱ የተባለው
የካቶሊክ ቄስ በኤርትራ አካባቢ ተዘዋውሮ ቅባትና ፀጋ የሚባሉ ፀረ
ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የምንፍቅና ትምሕርት አስተምሮ ብዙ ተከታዮችን አፍርቷል፤ ይህ እምነት አንዳንድ ጊዜ በግልጽ ሊላ ጊዜ በስውር
ሲስፋፋ ቆይቶ በአፄ ቴዎድሮስ፣ በአፄ ዮሐንስ እና በአፄ ምንሊክ ጊዜ ይሕንን እምነት የሚያራምድ ካሕን ወይም ምእመን ቢገኝ ከፍተኛ
ቅጣት እንደሚጠብቀው በማወጃቸው እምነቱን ከካቶሊክ ጋር ያለው ትስስር ሳይቋረጥ በሚስጥር ተዋቅሮዋል።
/የኢትዮጵያ
ከአፄ ልብነ ድንግል እስከ አፄ ቴዎድሮስ/ በተክለ ጻድቅ መኩሪያ
ገፅ 144
በአንደኛው
ሆነ በሁለተኛው የጣሊያን ወረራ ወቅት የዚህ እምነት ተከታዮች ካሕናትና ምእመኑ ለጣሊያን በባንዳነት አገልግለዋል። ዛሬ ሕውሀትን
የፈጠሩት ሰዎች አባቶቻቸው የታወቁ ባንዳዎች እንደሆኑ ሲታወቅ አምነታቸውም ፀረ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ከሆነው አፍቃሪ ካቶሊክ ጋር
የተያያዘ ነው። ቤተክርስቲያን ላይ ተሹመው ያሉ ጳጳሳትም አብዛኛዎቹ በዚሕ በሚስጥር ከሚንቀሳቀሰው አፍቃሪ ካቶሊክ አማኞች ናቸው።
ለዚህም ነው በቤተክርስቲያን ላይ የሚነሱ የተሀድሶና ሊሎች የኑፋቄ ትምሕርቶችን የሚያራምዱ ግለሰቦችን ሲኖዶሱ አውግዞ እንዲለያቸው
አልያም ከኑፋቅያቸው እንዲመለሱ አድርጉ ተብለው ሲጠየቁ ፍቃደኛ የማይሆኑት።
- የኢትዮጵያ ሙስሊሞችና
የሕውሀት ጠብ
ሕውሀት የኢትዮጵያን ሙስሊሞች
ለመያዝ በኦርቶዶክስ ክርስቲያን መንግስት ሲጨቆኑ እንደኖሩ አድርጎ ሲሰብክ ነበር፤ ቡዙ ሙስሊሞች ስብከቱ እውነት መስሏቻው ለረጅም
ጊዜ አምነው ተቀብለውት ነበር። በእምነታቸው ሙስሊም የሆኑ የክልል ባለስልጣናት ወያኔ የሚያራምደውን የጸረ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን
ትግል በመደገፍ ሕዝበ ክርስቲያኑን በማፈናቀል፣ ቤተክርስቲያን እንዳይሰራ በማገድ እና ኦርቶዶክስ ክርስቲያንኖች በክልሉ የመንግስት
መስሪያ ቤቶች ስራ እንዳይቀጠሩ በማድረግ የወያኔን አላማ በፍቃደኝነት ሲያራምዱ ቆይተዋል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የእስልምና መሪዎችን በራሱ ፍቃድ በመምረጡ በሙስሊሙ ማሕበረ ሰብ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሞታል። ይህ
ተቃውሞ እየተጠናከረ በሀገር ውስጥ ሆነ ከሀገር ውጪ አድማሱን አስፍቷል፤
እስካሁን የኢትዮጵያ ሙስሊሞች እያደረጉት ያለው ተቃውሞ ሰላማዊ ሲሆን ትግላቸው በሀይል የታገዘ ቢሆን በቀላሉ ሕውሀት የሀይማኖት
ነጻነት ትግላቸውን ሊላ ትርጉም በመስጠት ትግሉን ለማዳፈን አለማቀፍ ድጋፍ ያስገኝለት ነበር።
ይህ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የእምነት ነጻነት ሰላማዊ ትግል ወደሌላ አቅጣጫ እንዳያመራ በመፍራት አንዳንድ ኦርቶዶክስ
ክርስቲያን ስጋታቸውን በተለያየ መንገድ ሲገልጹ ይሰማል፤ ነገር ግን ይህ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖችን በፍጹም ስጋት ውስጥ ሊከት አይገባም
ይልቅስ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን ለ25 ዓመታት የሀይማኖት ነጻነታችንን ለተነጠቅንና ለተገፋን ከኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የነጻነት ትግል በመማር እኛም ስለ ሀይማኖታችን ነጻነት
ሁለገብ ትግል በተቀናጅ መልኩ ልናደርግ ይገባል።
- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስቲያኖች የነጻነት ትግል እና የፓለቲካ ስልጣን ጥያቄ
ከላይ በተለያዩ ርእሶች
እንዳየነው የሕውሀት መንግስት ኦርቶዶክስ ክርስቲያን ጨቁኖና የእምነት ነጻነት አሳጥቶ እንዳለ ይታወቃል፤ ኦርቶዶክስ ክርስቲያንኖች
ሕልውናቸው የሚረጋገጠው በቅድሚያ ቤተክርስቲያናችንን ከወያኔ ስርአት ታግለን ነጻ ማድረግ ስንችል ነው። ይህ የኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች
የነጻነት ትግል ማንኛውንም አማራጭ መጠቀም የሚያስችል ይሆናል፤ የነጻነት ትግል ለማድረግ የተጨቆነው አካል ነው የነጻነት ትግሉን
በምን መልክ መሆን እንደሚገባው መወሰን የሚገባው። ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች እራሳቸውን ሆነ ቤተክርስቲያናቸውን ነጻነት እንዴት
መታገል እንዳለባቸው የአባቶቻቸውን ታሪክ ማወቅ ይኖርባቸዋል።
ሊላው በአለማችን ላይ ሕዝቦች ሀይማኖታቸውን መሰረት አድርገውና ተደራጅተው
ለዲሞክርሲያዊ የፖለቲካ ስልጣን ይወዳደራሉ። በተለይ በአደጉና ዲሞክራት ሀገራት በሀይማኖት ማንነታቸው የተደራጁ የፖለቲካ ፓርቲዎች
ቁጥራቸው ቀላል አይደሉም። ለምሳሌ፦
·
Germany- (ገዥው)
Christian democratic union of Germany, Christian social union in Bavaria.
·
Netherlands-
Christian democratic appeal, Christian union.
·
Russia-
Christian democratic party of Russia.
·
United
States- Christian democratic union of the United States.
·
United
Kingdom- Christian Democratic Party, Christian Party, Christian People’s
Alliance, The Common Good (Political Party).
አነዚህ ከላይ ለምሳሌ ያየናቸው ሀገራት በሀይማኖታቸው የተደራጁ
የፖለቲካ ፓርቲዋች ለስልጣን እንዲወዳደሩ ሕገመንግስታቸው ያዛል። አሁን ያለው የወያኔ ሕገመንግስት በቋንቋ ማንነት ላይ የተደራጁ
ፖለቲካ ፓርቲዎች ወደ ስልጣን እንዲመጡ ሲፍቅድ ከላይ እንዳየነው በየትኛውም የዲሞክራሲ ሀገራት የሚፈቀደውን በሀይማኖት ማንነት
ለፖለቲካ ስልጣን መደራጀትን ወያኔ በሕገ መንግስቱ አንቀጽ11 እና 27 ላይ አግዶታል።
የኢትዮጵያ
ሕዝብ ከየትኛውም የአለም ሕዝብ በተሻለ ሀይማኖተኛ ሕዝብ ነው፤ ታሪኩም እንደሚያሳየው ኢትዮጵያን ይገዙ የነበሩት ነገስታት ከማንኛውም
ማንነት የሀይማኖት ነገር ከፍተኛውን ቦታ ይይዛል። በኢትዮጵያ ሀይማኖቶች ወደ ፖለቲካ ስልጣን መምጣት አሁን በማን አለብኝነት ተወጥሮና
ገዝፎ የሚታየውን ከቋንቋ ማንነት አልፎ ወደዘርና ቢሔር የተቀየረውንና ሀገራችንን አደጋውስጥ የጣለው ፓለቲካ የሚያስተነፍስ ይሆናል።
በሕውሀት የረቀቀው የሀገሪቱ ሕገመንግስት በዓለም ላይ ዋና ከሆነው
የዲሞክራሲ መርሆች አንዱ የሆነው በዲሞክራሲያዌ መንገድ በነጻነት
በተለያየ መንገድ የመደራጀትን መብት በጣሰ መልኩ የሀይማኖት ማንነትን
መሰረት አድርጎ ለፖለቲካ ስልጣን መደራጀትን የሚከለክል ሕግ ደንግጓል። ይህ ሕግ በአለም ላይ ባሉ ዲሞክራቲክ ሀገራት ላይ የማይሰራ መሆኑን ለአብነት
ከላይ ለምሳሌነት የቀረቡ ሀገራትን ማየት ይቻላል። ሕውሀት አስቀድሞ ይህንን ነጻነት የነፈገበት ምክንያት ኢትዮጵያውያን ለእምነታቸው
ያላቸውን ትልቅ ክብር በመረዳት በእምነት ለፖለቲካ ስልጣን መደራጀት እነሱ የመጡበትን ቋንቋን መሰረት ያደረገ ፖለቲካን ተቀባይነት
እንደሚያሳጣው አስቀድመው ስለተረዱ ነው።
አሁን በተለይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስቲያኖች ከወያኔ የጭቆና ስርአት
ነጻ ለመውጣት አለማቀፋዊ በሆነው የዲሞክራሲ መርሕ በነጻነት ለፖለቲካ
ስልጣን መደራጀት መብታቸው እንደሆነ አውቀው ሕውሀት በሀገሪቱ ሕገመንግስት ላይ አደናብሮ ያስቀመጠውን ሀይማኖት በፖለቲካ ውስጥ
ያለመግባት ሕግ በመቃወም እንዲነሳ እና በሀገራችን ዲሞክራሲያዊ ስርአት እንዲሰፍን መታገል ይኖርባቸዋል።