Sunday, August 21, 2016

ሰማእትነትን ከሸሹት ሰማእት ሊኖር አይችልም


        አንዳንድ ሰባክያን ጥንት እንጂ አሁን ሰማእትነት የለም እያሉ ያስተምራሉ፡፡ ሰባክያኑ ቄሳርን ፈርተው ቄሳርን የማያስቆጣ ነገር ካልተናገሩ በየት ሰማእትነት ያገኛቸዋል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሀገሩ ከልዳ ተነስቶ ፋርስ ድረስ ሄዶ የአንድ ሳይሆን የሰባ ነገስታትን ግርማ ሳይፈራ በጀግነት ስለሀይማኖቱ ስለመሰከረ ከሰማእታት ሁሉ የበለጠ የሰማእትነት ክብር አግኝቷል፡፡ ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥም ሰማእትነት አለ ክርስቲያኖች በሰይፍ ይታረዳሉ፣ በእሳት ይቃጠላሉ፣ ከቀያቸው ይፈናቀላሉ ንብረታቸውን ይዘረፋሉ  ታድያ ይህንን በአይናቸው እያዩ ሽምጥጥ አድርገው ዛሬ ሰማእትነት የለም ከራስ ጋር መታገል ነው እያሉ በድፍረት ይናገራሉ፡፡

          በ17ተኛው ክፍለ ዘመን በኢትዮጵያ ታሪክ የኢትዮጵያ ንጉስ የነበሩት አጼ ሲስንዮስ የተዋህዶ እምነታቸውን ቀይረው ካቶሊክ ሲሆኑና የካቶሊክን እምነት በኢትዮጵያ ለማስፋፋት ሲሞክሩ ይህንን ስራቸውን የተቃወሙ ‹‹ አንተ በኢትዮጵያ ምድር እውነተኛውን እምነት ትተህ የባእድ እምነት አምነህ በኢትዮጵያ ላይ መሪ አትሆንም›› ብለው በመቃወማቸው ካህናቱ፣ ጳጳሱ፣ ምእመናኑ፣ እና መኳንንቱ በሰማእትነት አልፈዋል፡፡ እነሱ በከፈሉት ሰማእትነት ቤተክርስቲያን ህያው ሆና እስካሁን ደርሳለች፡፡

        አሁን በኢትዮጵያ ካቶሊክ አይደለም እግዚአብሔርን የማያምን (ፓጋን) መሪ ተቀምጦ ደሐ ሲበድል፣ ክርስቲያኖችን ሲያሳድድ፣ ቤተክርስቲያንን ሲያስቃጥል፣ የቤተክርስቲያንን ንብረት ቅርስ ሲያዘርፍ፤ ጳጳሳቱ፣ ሰባክያኑ  ካልተናገሩና ካልተቃወሙ ከየት ሰማእትነት ይመጣል፡፡ እስካሁን እንዳየነው ምእመናኑ እና ካህናቱ ታረዱ፣ ተገደሉ፣ ከቀያቸው ተፈናቀሉ፣ ንብረታቸው ተዘረፈ፣ ፍርድ ተጓደለባቸው ሲባል ሰምተናልም አይተናልም ፡፡ ነገር ግን  አንድም ጳጳስ እና ሰባኪ ታሰረ፣ ተገደለ ተብሎ ሲናገርም አልሰማንም አላያንም ሊላው ቀርቶ በስደት ያሉት ሰባክያን ኢትዮጵያ ውስጥ ስላላቸው ንብረት እና ቤተሰቦቻቸው እያሰቡ ስለ ቄሳር ማንሳት አይፈልጎም፡፡

        ንጉስ አክሀብ የደሀውን የናቡቴን መሬት ለመውረስ የናቡቴን ደም አፈሰሰ፡፡ የእግዚአብሔር ሰዎች የደሀው ደም ሲፈስ ዝም ብለው አያዩምና በወቅቱ ነብይ የነበረው የእግዚአብሔር ሰው ኤልያስ ተነስቶ ንጉሱን አክአብን ተቃወመው፡፡ ስላደረገውም በደል በሱ ላይ ተመሳሳይ ቅጣት እደሚያገኘው ነግሮታል፡፡ ዛሬ በሀገራችን ደሀው በችግር ተቆራምዶ፣ ቤቱ ንብረቱ መሬቱ እየተወረሰ፣ ፍርድ አቶ የዳኛ ያለህ እያለ፤ ያም ሳይበቃ እንደ ራሔል እናት  ልጆቿን በቄሳር ወታደሮች ተገለውባት እምባዋን ወደ ራማ በምትረጭበት ወቅት ጳጳሳቱና ሰባክያኑ በህዝቡ ገንዘብ ኑሮዎቸውን እየደጎሙ ይልቁንም ቄሳርን እያመሰገኑና ሰማእትነት የለም ሁሉም ሰላም ነው እያሉ ተቀምጠዋል፡፡ ይዘገያል እንጂ የደሀው ጭሆት የናቶች እንባ ጽዋው ሞልቶ ወደ እግዚአብሔር ደርሶ መልስ ይዞ መምጣቱ አይቀርም፡፡ የቤተክርስቲያንን አገልግሎት እንጀራ ያደረጉት ጳጳሳትና ሰባክያን የት ይደርሱ ይሆን፡፡

        

Wednesday, July 13, 2016

ወዮ ለትግራይ!


ወዮ ለትግራይ!

             በትግራይ መንገዶች እየተመላለሳችሁ ሩጡ ተመልከቱም እወቁም በአደባባይዋም ፈልጉ ፍርድን የሚያደርገውን እውነትንም የሚሸውን ሰው ታገኙ እንደሆነ ይቅር እላታለሁ። እነርሱም ሕያው እግዚአብሔርን! ቢሉ የሚምሉት በሐሰት ነው። አቤቱ ዓይንህ እውነትን የምትመለከት አይደለችምን? አንተ ቀሰፈሃቸዋል ነገር ግን አላዘኑም ቀጥቅጠሃቸዋል ነገር ግን ተግሣጽን እንቢ አሉ ፊታቸውን ከድንጋይ ይልቅ አጠንክረዋል ይመለሱ ዘንድ እንቢ አሉ።

          እኔም የእግዚአብሔርን መንገድ የአምላካቸውን ሕግ አላወቁምና እነዚህ በእውነት ድሆችና ሰነፎች ናቸው፤ ወደ ታላላቆቹም ካሕናትና ጳጳሳት እሄዳለሁ አናገራቸውማለሁ የእግዚአብሔርን መንገድ የአምላካቸውን ሕግ ያውቃሉና አልሁ። አነዚህ ግን ቀንበሩን በአንድነት ሰብረዋል እስራቱንም ቆርጠዋል። ስለዚህ ሀጢአታቸው በዝቶአልና የክዳታቸውም ብዛት ጸንቶልና ስለዚህ አንበሳ ከዱር ወጥቶ ይሰብራቸዋል የበረሀም ተኩላ ያጠፋቸዋል ነብርም በከተማቸው ላይ ይተጋል ከዚያም የሚወጣ ሁሉ ይነጠቃል።

          ትግራይ ሆይ በእነዚህ ነገሮች ይቅር የምልሽ እንዴት አድርጌ ነው? ልጆችስ ትተውኛል አማልክትም ባልሆኑ ምለዋል ካጠገብሀቸው በሗላ አመነዘሩ በጋለሞቶችምቶቹም ቤት ተሰበሰቡ። እንደ ተቀለቡ ፈረሶች ሆኑ፤ እያንዳንዳቸውም ከባልንጀሮቻቸው ሚስቶች ሗላ አሽካኩ። በውኑ ስለ እነዚህ ነገሮች አልቀሥፍምን? ይላል እግዚአብሔር ነፍሴስ እንደዚህ ባለ ሕዝብ ላይ አትበቀልምን? የትግራይ ልጆች እጅግ ወንጅለዋል ይላል እግዚአብሔር። እነሱም ክፉ ነገርም አይመጣብንም ሰይፍንና ራብንም አናይም።

          ስለዚህም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ትግራይ ሆይ እነሆ ሕዝብን ከሩቅ አመጣባችሀለው ፣ ሀያል ጥንታዊ ሕዝብ ነው ቋንቋቸውንም የማታውቀው የሚናገሩትንም የማታስተውለው ሕዝብ ነው። የሰይፋቸውም ሰገባ እንደተከፈተ መቃብር ነው፣ ሁሉም  ሀያላን ናቸው። መከርህንና እንጀራህን ይበላሉ፣ ወንዶችና ላሞችህንም ይበላሉ በለስህንም ይበላሉ የምትታመናቸውን የተመሸጉ ከተሞችን በሰይፍ ይደበድባሉ። እንዲህ ይሆናል እናንተ አምላካችን እግዚአብሔር ይህን ነገር ሁሉ ስለምን አደረገብን ብትሉ እናንተ እደተዋችሁኝ በአገራችሁም ሌሎችን አማልክት እንዳመለካችሁ እንዲሁ ለእናንተ ባልሆነ አገር ለሌሎች ሰዋች ትገዛላችሁ።

         እናንተ ሰነፎች ልበ ቢሶች ዓይን እያላችሁ የማታዩ ጆሮም እያላችሁ የማትሰሙ የትግራይ ሕዘብ ሆይ ይህን ስሙ። በውኑ እኔን አትፈሩምን? ከፊቴስ አትደነግጡም ? ይላል እግዚአብሔር ። በናተ መካከል ክፉዎች ሰዎች ተገኝተዋል እንደ አጥማጆችም ያደባሉ ወጥመድንም ይዘረጋሉ ሰዋችንም ያጠምዳሉ። ቀፎ ወፎችን እንደሚሞላ እንዲሁም ቤታቸው ሽንገላን ሞልታለች፤ እንዲሁም ከብረዋል ባለጠጎችም ሆነዋል ወፍረዋል ሰብተውማል ክፋታቸውንም ያለ ልክ አብዝተዋል የድሀ አደጎች ነገር መልካም ፍርድ አልፈረዱላቸውም። በውኑ ስለ እነዚህ ነገሮች አልቀስፍምን? ይላል እግዚአብሔር ነፍሴስ እንደዚህ ባለ ሕዝብ ላይ አትበቀልምን?

         የምታስደንቅና የምታስደነግጥ ነገር በምድር ላይ ሆናለች ጳጳሳት በሐሰት ይናገራሉ ካህናትም በእነዚህ እጅ ይገዛሉ ሕዝቡም እንዲህ ያለውን ነገር ይወዳሉ ከፍጻሜውስ ምን ታደርጋላችሁ? እናንተ የትግራይ ልጆች ክፉ ነገር ታላቅም ጥፋት ከሰሜን ይጎበኛልና ከትግራይ ሽሹ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ዛፎቿዋን ቁረጡ በከተማ አፈርን ደልድሉ ትግራይ የምትቀሰፍ ናት መካከልዋ ሁሉ ግፍ ብቻ  ነው። ከጉድጓድ ውሃ እንደሚፈልቅ እንዱሁ ክፋትዋ ከእርስዋ ዘንድ ይሰማል ደዌና ቁስልም ሁልጊዜ በፌቴ አለ። ትግራይ ሆይ ነፍሴ ካንች እንዳትለይ አንችንም ባድማና ወና እንዳላደርግሽ ተግሣጽን ተቀበይ።

         ትሰማኝ ዘንድ ለማን እናገራለሁ ? ለማንስ አስጠነቅቃለሁ? እነሆ ጆሮአቸው ያልተገረዘች ናት ለመስማትም አይችሉም እነሆ የእግዚአብሔር ቃል ለስድብ ሆኖባቸዋል ደስም አያሰኛቸውም ። ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ስስትን ያስባሉና፤ ከጳጳሳት ጀምሮ እስከ ካህናት ድረስ ሁሉ በተንኮል ያደርጋሉና። ሰላም ሳይሆን ሰላም ሰላም ይላሉ። ርኩሰት ነገር ስለ ሠሩ አፍረዋልን? ምንም አላፈሩም እፍረትንም አላወቁም ስለዚህ ከሚወድቁ ጋር ይወድቃሉ በጎበኘሀቸው ጊዜ ይዋረዳሉ ይላል እግዚአብሔር።

        እግዚአብሔር እንዲህ ይላል በመንገድ ላይ ቁሙ ተመልከቱም የቀደመች የአባቶቻችሁን መንገድ ጠይቁ መልካሚቱ መንገድ ወዴት እንደሆነች እወቁ በእርስዋም ላይ ሂዱ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ እነርሱ ግን አንሄድባትም አሉ።

         እነሆ በዚህ ሕዝብ ፊት እንቅፋቶችን አደርጋለሁ አባቶችና ልጆች በአንድነት ይሰናከሉባቸዋል፣ ጎረቤትና ባልንጀራም ይጠፈሉ። እነሆ ሕዝብ ከሰሜን አገር ይነሣል ቀስትንና ጦርን ይይዛሉ ጨካኞች ናቸው። ምሕረትም አያደርጉም ድምፃቸው እንደ ባሕር ይተማል በፈረሶችም ላይ ይቀመጣሉ፤ የትግራይ ሴት ሆይ ማቅ ልበሺ በአመድም ውስጥ ተንከባከይ አጥፊ በላይሽ በድንገት ይመጣል በአንድያ ልጅ እንደሚደረግ ልቅሶ መራራ ልቅሶ አልቅሺ።

         የትግራይ ሕዝብ ሆይ እነሆ በማትረቡበት በሐሰት ቃል ታምናችሀል፤ ትሰርቃላችሁ ትገድላላችሁ ታመነዝራላችሁ በሐሰትም ትምላላችሁ የማታውቋቸውንም እንግዶች አማልክት ትከተላላችሁ መጥታችሁም ስሜም በተጠራበት በዚህ ቤት በፌቴ ቆማችሁ ይህን አስጸያፊ የሆነ ነገርን ሁሉ አላደረግንም አላችሁ። ይህስ ስሜ የተጠራበት ቤት በዓይናችሁ የሌቦች ዋሻ ሆኖአልን? እነሆ አይቻለሁ ይላል እግዚአብሔር።

        የዚህም ሕዝብ ሬሳ በሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት መብል ይሆናል የሚያስፈራራቸውም የለም። ምድሪቱም ባድማ ትሆናለችና ከትግራይ ከተሞች አደባባይ የእልልታን ድምፅና የደስታን ድምፅ የወንድ ሙሽራን ድምፅና የሴት ሙሽራ ድምፅ አጠፋለሁ።

         እግዚአብሔር እንዲህ ይላል የወደቁ አይነሱምን? የሳተስ አይመለስምን? እንግዲህ ይህ የትግራይ ሕዝብ ዘወትር ስለ ምን ወደ  ሗላው ይመለሳል? ተንኮልን ይዞአል ሊመለስም እንቢ ብሎአል። አዳመጥሁ ሰማሁም ቅንን ነገር አልተናገሩም ማናቸውም ምን አድርጌለሁ? ብሎ ከክፋቱ ንሰሐ የገባ የለም ወደ ሰልፍም እንደሚሮጥ ፈረስ እያንዳንዱ በየመንገዱ ይሄዳል። ሽመላ በሰማይ ጊዜዋን አውቃለች፣ ዋኖስና ጨረባ፣ ዋልያም የመምጣታቸውን ጊዜ ይጠብቃሉ፤ የትግራይ ሕዝብ ግን የእግዚአብሔርን ፍርድ አላወቀም።