Monday, August 29, 2016
Sunday, August 21, 2016
ሰማእትነትን ከሸሹት ሰማእት ሊኖር አይችልም
አንዳንድ ሰባክያን ጥንት እንጂ አሁን ሰማእትነት የለም እያሉ ያስተምራሉ፡፡ ሰባክያኑ ቄሳርን ፈርተው ቄሳርን የማያስቆጣ
ነገር ካልተናገሩ በየት ሰማእትነት ያገኛቸዋል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሀገሩ ከልዳ ተነስቶ ፋርስ ድረስ ሄዶ የአንድ ሳይሆን የሰባ
ነገስታትን ግርማ ሳይፈራ በጀግነት ስለሀይማኖቱ ስለመሰከረ ከሰማእታት ሁሉ የበለጠ የሰማእትነት ክብር አግኝቷል፡፡ ዛሬ ኢትዮጵያ
ውስጥም ሰማእትነት አለ ክርስቲያኖች በሰይፍ ይታረዳሉ፣ በእሳት ይቃጠላሉ፣ ከቀያቸው ይፈናቀላሉ ንብረታቸውን ይዘረፋሉ ታድያ ይህንን በአይናቸው እያዩ ሽምጥጥ አድርገው ዛሬ ሰማእትነት የለም ከራስ
ጋር መታገል ነው እያሉ በድፍረት ይናገራሉ፡፡
በ17ተኛው ክፍለ ዘመን በኢትዮጵያ ታሪክ የኢትዮጵያ ንጉስ የነበሩት አጼ ሲስንዮስ የተዋህዶ እምነታቸውን ቀይረው ካቶሊክ
ሲሆኑና የካቶሊክን እምነት በኢትዮጵያ ለማስፋፋት ሲሞክሩ ይህንን ስራቸውን የተቃወሙ ‹‹ አንተ በኢትዮጵያ ምድር እውነተኛውን እምነት
ትተህ የባእድ እምነት አምነህ በኢትዮጵያ ላይ መሪ አትሆንም›› ብለው በመቃወማቸው ካህናቱ፣ ጳጳሱ፣ ምእመናኑ፣ እና መኳንንቱ በሰማእትነት
አልፈዋል፡፡ እነሱ በከፈሉት ሰማእትነት ቤተክርስቲያን ህያው ሆና እስካሁን ደርሳለች፡፡
አሁን በኢትዮጵያ ካቶሊክ አይደለም እግዚአብሔርን የማያምን (ፓጋን) መሪ ተቀምጦ ደሐ ሲበድል፣ ክርስቲያኖችን ሲያሳድድ፣
ቤተክርስቲያንን ሲያስቃጥል፣ የቤተክርስቲያንን ንብረት ቅርስ ሲያዘርፍ፤ ጳጳሳቱ፣ ሰባክያኑ ካልተናገሩና ካልተቃወሙ ከየት ሰማእትነት ይመጣል፡፡ እስካሁን እንዳየነው
ምእመናኑ እና ካህናቱ ታረዱ፣ ተገደሉ፣ ከቀያቸው ተፈናቀሉ፣ ንብረታቸው ተዘረፈ፣ ፍርድ ተጓደለባቸው ሲባል ሰምተናልም አይተናልም
፡፡ ነገር ግን አንድም ጳጳስ እና ሰባኪ ታሰረ፣ ተገደለ ተብሎ ሲናገርም
አልሰማንም አላያንም ሊላው ቀርቶ በስደት ያሉት ሰባክያን ኢትዮጵያ ውስጥ ስላላቸው ንብረት እና ቤተሰቦቻቸው እያሰቡ ስለ ቄሳር
ማንሳት አይፈልጎም፡፡
ንጉስ አክሀብ የደሀውን የናቡቴን መሬት ለመውረስ የናቡቴን ደም አፈሰሰ፡፡ የእግዚአብሔር ሰዎች የደሀው ደም ሲፈስ ዝም
ብለው አያዩምና በወቅቱ ነብይ የነበረው የእግዚአብሔር ሰው ኤልያስ ተነስቶ ንጉሱን አክአብን ተቃወመው፡፡ ስላደረገውም በደል በሱ
ላይ ተመሳሳይ ቅጣት እደሚያገኘው ነግሮታል፡፡ ዛሬ በሀገራችን ደሀው በችግር ተቆራምዶ፣ ቤቱ ንብረቱ መሬቱ እየተወረሰ፣ ፍርድ አቶ
የዳኛ ያለህ እያለ፤ ያም ሳይበቃ እንደ ራሔል እናት ልጆቿን በቄሳር ወታደሮች ተገለውባት እምባዋን ወደ ራማ በምትረጭበት
ወቅት ጳጳሳቱና ሰባክያኑ በህዝቡ ገንዘብ ኑሮዎቸውን እየደጎሙ ይልቁንም ቄሳርን እያመሰገኑና ሰማእትነት የለም ሁሉም ሰላም ነው
እያሉ ተቀምጠዋል፡፡ ይዘገያል እንጂ የደሀው ጭሆት የናቶች እንባ ጽዋው ሞልቶ ወደ እግዚአብሔር ደርሶ መልስ ይዞ መምጣቱ አይቀርም፡፡
የቤተክርስቲያንን አገልግሎት እንጀራ ያደረጉት ጳጳሳትና ሰባክያን የት ይደርሱ ይሆን፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)